ለማግባት ዝግጁ ነህ?
አንድ ወንድ እድሜው ስለደረሰ ብቻ ለማግባት ዝግጁ ነው መባል አይችልም:: ማግባት ማለት በተሰብ መመስረት ብቻ ሳይሆን በተሰብ ማስተዳደርም ይጨምራል በሀገራችን ባህል መሰረት የበተሰብ አስተዳዳሪ መሆን የሚገባው ደሞ ባል ወይም ወንድ ነው::ቤተሰብ መስተዳደር ያለበት በአንድ ሰው ነው:: ይህ ሲባል ግን ሚስት ድርሻ የላትም ማለት አይደለም በምሳሌ ለማስረዳት ያህል ሀገር የሚያስተዳደር እና የሚመራ አንድ ሰው ነው መስራቤትንም ቢሆን የሚያስተዳደር አንድ ሰው ነው ሆኖም ሁሉም ረዳቶች ወይም ምክትል አስተዳዳሪዎች ኣሏችው::
ትዳርም ቢሆን ተመሳሳይ ነው አንድ አስተዳዳሪ ነው ሊኖረው የሚገባው ለዝህ ደሞ ሀላፊነቱን መውሰድ ያለበት ወንድ ነው ስለዝህ አንድ ውንድ ለማግባት ዝግጁ ነው የሚባለው ቢያንስ እነዝህን ሦስት ነገሮችን ሲያሟላ ነው እነሱም የትዳር አጋሩን ቁሳዊ፣ስሜታዊ እና መንፈሳዊ ነገሮችን ሲያሟላ ነው እስቲ እነዝህን አንድ በአንድ እንያችው
፩) ቁሳዊ ፍላጎት ሟሟላት!
አንድ ውንድ ከማግባቱ በፊት ሊያስብበት የሚገባው ነገር የትዳር አጋሬን ቁሳዊ ፍላጉት ማሟላት እችላልወ፧ የሚለውን ነው፥፥ ቁሳዊ ፍላጎት ስንል ከልብስ፣ መጠለያ እና ከምግብ በተጨማሪ እንደ ኮስሞቲክስ ያለ የሴቶች መዋቢያ ያሉ ወጪዎችም ያካትታል:: እንደ ትዳር ጓደኛው ባህሪ ቢለያይም አንድ ወንድ ከማግባቱ በፊት ከመሰረታዊ ፍላጎቶች
በተጨማሪ የባለቤቴን ቁሳዊ ፍላጎት ማሟላት እችላለው ቢሎ አራሱን መጠየቅ አለበት::
፪) ስሜታዊ ፍላጎት ሟሟላት
አንድ ወንድ ከማግባቱ በፊት የትዳር ጓደኛየን ስሜታዊ ፍላጎት አሟላለው ወይ ብሎ እራሱን መጠየቅ አለበት ስሜታዊ ፍላጎት ሲባል የጾታ ግኑኙነት ብቻ ሳይሆን አንደ መዝናኛ ያሉ ለምሳሌ ፊልም፣ ትያትር፣ሙዚቃ፣ ሰርፕራይዝ መደረግ ከጓደኞቿ ጋር ዘና እንድትል ማድረግ እና በማንኛውም ሁኔታ ሙሉ ትኩረትን መስጠት እና ሌሎችንም እነዚህን እንደ ምሳሌ ተነሱ እንጂ እንደ ትዳር ጓደኛው ባህሪ ሊለያይ ይችላል ስለዝህ አንድ ውንድ ወደ ትዳር ከመግባቱ በፊት የትዳር ጓደኛውን ስሜት መረዳት እና ስሜቷን ለሟሟላት ዝግጁ መሆኑን እራሱን መጠየቅ አለበት::
፫) መንፈሳዊ ፍላጎት ሟሟላት!
አንድ ወንድ ወደ ትዳር ከመግባቱ በፊት የትዳር አጋሬን መንፈሳዊ ፍላጎት አከብራለው ውይም ደሞ መንፈሳዊ ፍላጎቷን አሟላለው ብሎ እራሱን መጠየቅ አለበት፥፥ ይህ ነጥብ በጣም ሰፊና አከራካሪ ስለሆነ ጠለቅ ብዬ አልገባበትም ግን አንደዚህ ጹሁፍ አዘጋጅ ሀሳብ ከሆነ ግን ለአሁንም ሆነ ወደፊት ልጆች ከመጡ በሗላ ሊመጡ የሚችሉትን ችገሮች እና አለመግባባቶች ማስቀረት የሚቻለው ሁለቱም ተመሳሳይ እምነት ሲኖራችው ነው፥፥
ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱም ወደ ትዳር ከመግባታችው በፊት ስለ ግል ባህሪያቸው ቆም ብለው ማሰብ አለባችው አስቲ ምሳሌ እንመልከት አንተ ወይም አንቺ ከወላጆቻችሁ ወይም ከወንድም እና ከእህቶቻችሁ ጋር እያላችሁ ግኑኙነታችሁ እንዴት ነው? ብዙ ጊዜ ከእነሱ ጋር ስትነጋገሩ ራሳችሁን መቆጣጠር ያቅታችዎል? ምናልባትም ስሜትን የሚጉዳ የሽሙጥ አነጋገር ትጠቀማላችሁ? በዚህ ረገድ እነሱ ስለ እናንተ ቢጠየቁ ምን ይላሉ? የቤተሰባችሁን አባላት የምትይዝበት መንገድ የትዳር ጓደኛችሁን እንዴት እብደምትይዙ ይጠቁማል::
ለነገሮች ያላችሁ አመለካከት አዎንታዊ ነው ወይስ አሉታዊ ? ምክንያታዊ ናችሁ ወይስ ሁልጊዜ እኔ ያልኩት ካልሆነ ትላላችሁ? ውጥረት የሚፈጥር ሁኔታ ሲያጋጥማችሁ ነገሮችን በረጋ መንፈስ ማከናወን ትችላላችሁ? ትዕግሥተኛ ናችሁ?
በገንዘብ አያያዝ ረገድ እንዴት ናችሁ? ብዙ ጊዜ ትበደራላችሁ? በአንድ ሥራ ላይ መቆየት ትችላላችሁ? ካልሆነ ምክንያቱ ምንድን ነው? የሥራው ጸባይ ነው ወይስ የአሠሪህ ባሕርይ? ወይስ ማስተካከል የሚያስፈልጋችሁ አንዳንድ መጥፎ ባሕርያት ወይም ልማዶች አሉ?
አንድዮሽ አማካሪና አገናኝ ኤጀንሲ በሃገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ፍቺ ለመቀነስ እና አንድ ሰው ወደ ትዳር ከመግባቱ በፊት ምክር የሚለግሱ ከሃገር ውስጥ እና ከውጪ ባለሞያዎች በመያዝ እናንተን ለመርዳት ዝግጅቱን አጠናቋል!!
በጋብቻ ዙሪያ ማንኛውም ጥያቄ ካላችው
በትዳር ውስጥ ሆናችው ምክር የምትፈልጉ info@wubtidar.com
ለአዲስ ትዳር መስራቾች የምክር አገልግሎት support@andyosh.com
አንድዮሽ ትዳር አማካሪ
We write rarely, but only the best content.
Please check your email for a confirmation email.
Only once you've confirmed your email will you be subscribed to our newsletter.