ትዳር መመስረት ይፈልጋሉ?
ብዙ ሰዋች እድሜያቸው ለጋብቻ ስለደረሰ ብቻ ትዳር መመስረት ይፈልጋሉ ግን ትዳር ለመመስረት መፈለግ እና ለትዳር ብቁ መሆን ይለያያል። ትዳር ሁለት የሚዋደዱ ጥንዶች በክፉም ሆነ በጥሩ ጊዜ ሳይለያዩ እስከ እድሜያችው መጨረሻ ድረስ አብረው የሚዘልቁበት መዋቅር ነው። በህይወታችን ከምናደርገው ከባድ እና አስፈላጊ ውሳኔዎች መሃከል ትዳር አንዱ እና ዋንኛው ነው::