Our Mission
በሃገራችንም ሆነ በአለም ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የፍቺ ቁጥር ለመቀነስ ብሎም ማንኛውም ሰው ወደ ትዳር ከመግባቱ በፊት ስለ ትዳር እና የትዳር ጔደኛ አመራረጥ የሚማርበት ድህረ ገፅ ነው።
በህይወታችን ከምናደርገው ከባድ እና አስፈላጊ ውሳኔዎች መሃከል ትዳር አንዱ እና ዋንኛው ነው::
ትዳር መመስረት ይፈልጋሉ?
ብዙ ሰዋች እድሜያቸው ለጋብቻ ስለደረሰ ብቻ ትዳር መመስረት ይፈልጋሉ ግን ትዳር ለመመስረት መፈለግ እና ለትዳር ብቁ መሆን ይለያያል። ትዳር ሁለት የሚዋደዱ ጥንዶች በክፉም ሆነ በጥሩ ጊዜ ሳይለያዩ እስከ እድሜያችው መጨረሻ ድረስ አብረው የሚዘልቁበት መዋቅር ነው።
አብዛኛዎቻችን ይህንን ውሳኔ የምናደርገው በስሜት ተገፋፍተን ወይም ማግባት ብቻ ሰላለብን የምናገባ አለን። ለዝህ ነው የፊቺ ቁጥር በየአመቱ እየጨመረ ያለው። እስቲ አንድ ምሳሌ እንመልከት መኪና መንዳት ከመጀመራችን በፊት እንዴት እንደሚነዳ መማር አለብን ከዚያም በኋላ መንዳት ስለቻልን ብቻ እንደፈለግን ማሽከርከር አንችልም ምክንያቱም የመንገድ ትራፊክ ህጎችን መከተል አለብን። ልክ እንደዝሁ ትዳርም ከመመስረታችን በፊት ስለትዳር ምንነት መማር እና በትዳር ውስጥ መከበር ስላለባችው ህጎች ማወቅ አለብን።
ለዝህ ደሞ አንድዮሽ ድህረ ገፅ አናንተን ለማስተማር በማህበራዊ ህይወት፣ በፍልስፍና እና በመንፈሳዊ ብቁ ከሆኑ ባለሞያዎች ጋር በመተባበር የተከፈተ ድህረ ገፅ ነው ። በተጨማሪም እውነተኛ የትዳር ጓደኛ ማግኘት ከፈለጋችሁ www.andyosh.com ን በመጫን መመዝገብ ትችላላችሁ፥፥ መልካም መተዋወቅ፦.
We write rarely, but only the best content.
Please check your email for a confirmation email.
Only once you've confirmed your email will you be subscribed to our newsletter.